Peace that given from heaven

I give you peace, the kind of peace that only I can give. It isn’t like the peace that this world can give. So don’t be worried or afraid.

John 14:27

እንደሚታስቡት የጦርነት ደጋፊ አይደለሁም። በፍጹም። ነገር ግን እናንተም እንደሚታስቡት ምዕራባዊያን እና አሜሪካ ለእኩልነት እና ለነጻነት የሚሟገቱ ሳይሆኑ ራሳቸውን ከሌላው የተሻለ አድርገው የሚቆጥሩ፣ በአንድ ወቅትም አፍሪካን እንደ ቅርጫ የተከፋፈሏት፣ ክብራችንን አዋርደው ለባርነት የማገዱን የክፋት ምንጮች ናቸው። አሁን የስልጣኔ ዘመን ነው በምንልበት በዚህ ወቅት እንኳን በተለያየ ሰንሰለት በዘመናዊ የባርነት ቀለበት ውስት አስገብተውናል። በእርዳታ ሰበብ፣ በኃይማኖት ሰበብ፣ በዲሞክራሲ ሰበብ መሸቀያቸው ከመሆን አልተረፍንም። ጠንካራ መሪዎቻችንን አጥፍተዋል። ሀብት ንብረታችንን ዘርፈዋል። አሁንም እየሞትን እንቀጥል?

ስለዚህ ጦርነትን ባልደግፍም ለነጻነቱ የሚታገል ሰው ግን አልተሳሳተም። ባህልህን፣ ቋንቋህን፣ ዕሴትህን በዘመንኛው ስልጣኔ እያወደሙ በምትኩ የራሳቸውን እያላበሱ ወረራ አድርገዋል። ኃይማኖቱ የአንተን አለባበስ እንደ እርኩስ የነሱን እንደ ጽድቅ ተርጉሟል። ትምህርቱ የነሱ ትክክለኛ የእኛ ሀገር በቀል እውቀት የፉገራ ሆኗል። እኔ መርጨ ባልተወለድኩት ማንነት ማፈርም መሸማቀቅም የለብኝም። አላደርገውምም።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚያንጸባርቀው ማንኛውም እይታ ልትከፉም ልትጎዱም አይገባም። እኔን ስለሚትወዱኝ እና እናንተ ይኸ ይሻላል በሚትሉት ቦታ ብቻ እንዲገኝ ከጠበቃችሁ ምናልባት ላንግባባ እንችላለን።

አቋሜ አንድ ነው። ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል። ሰው ሁሉ እኩል ነው። ማንም ከማንም አይበልጥም አያንስም። ከዚህ አቋሜ ዝንፍ አልልም።

ነገር ግን በኃይማኖት ወይም መንፈሳዊ ትርጓሜ እየሰጣችሁ ሰዎች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ዕሴታቸውን እንዳያንጸባርቁ የስነልቦና ጫና ለሚትፈጥሩ ጆሮ የለኝም። እግዚአብሔር በሁሉም ባህል ይከብራል፣ ይከበራል። በሁሉም ቋንቋ ይመለካል። ይሰማል።

የትኛው ቋንቋ ነው ትክክል? የትኛው አጨፋፈር ነው ትክክል? የትኛው አለባበስ ነው ትክክል? ሁሉም ተጠቅልለው የዚህ ዓለም ናቸው። ሐይማኖትም በዚህ ዓለም ይቀራል።

May be a black-and-white image of 1 person and indoor