Peace that given from heaven

I give you peace, the kind of peace that only I can give. It isn’t like the peace that this world can give. So don’t be worried or afraid.

John 14:27

እንደሚታስቡት የጦርነት ደጋፊ አይደለሁም። በፍጹም። ነገር ግን እናንተም እንደሚታስቡት ምዕራባዊያን እና አሜሪካ ለእኩልነት እና ለነጻነት የሚሟገቱ ሳይሆኑ ራሳቸውን ከሌላው የተሻለ አድርገው የሚቆጥሩ፣ በአንድ ወቅትም አፍሪካን እንደ ቅርጫ የተከፋፈሏት፣ ክብራችንን አዋርደው ለባርነት የማገዱን የክፋት ምንጮች ናቸው። አሁን የስልጣኔ ዘመን ነው በምንልበት በዚህ ወቅት እንኳን በተለያየ ሰንሰለት በዘመናዊ የባርነት ቀለበት ውስት አስገብተውናል። በእርዳታ ሰበብ፣ በኃይማኖት ሰበብ፣ በዲሞክራሲ ሰበብ መሸቀያቸው ከመሆን አልተረፍንም። ጠንካራ መሪዎቻችንን አጥፍተዋል። ሀብት ንብረታችንን ዘርፈዋል። አሁንም እየሞትን እንቀጥል?

ስለዚህ ጦርነትን ባልደግፍም ለነጻነቱ የሚታገል ሰው ግን አልተሳሳተም። ባህልህን፣ ቋንቋህን፣ ዕሴትህን በዘመንኛው ስልጣኔ እያወደሙ በምትኩ የራሳቸውን እያላበሱ ወረራ አድርገዋል። ኃይማኖቱ የአንተን አለባበስ እንደ እርኩስ የነሱን እንደ ጽድቅ ተርጉሟል። ትምህርቱ የነሱ ትክክለኛ የእኛ ሀገር በቀል እውቀት የፉገራ ሆኗል። እኔ መርጨ ባልተወለድኩት ማንነት ማፈርም መሸማቀቅም የለብኝም። አላደርገውምም።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚያንጸባርቀው ማንኛውም እይታ ልትከፉም ልትጎዱም አይገባም። እኔን ስለሚትወዱኝ እና እናንተ ይኸ ይሻላል በሚትሉት ቦታ ብቻ እንዲገኝ ከጠበቃችሁ ምናልባት ላንግባባ እንችላለን።

አቋሜ አንድ ነው። ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል። ሰው ሁሉ እኩል ነው። ማንም ከማንም አይበልጥም አያንስም። ከዚህ አቋሜ ዝንፍ አልልም።

ነገር ግን በኃይማኖት ወይም መንፈሳዊ ትርጓሜ እየሰጣችሁ ሰዎች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ዕሴታቸውን እንዳያንጸባርቁ የስነልቦና ጫና ለሚትፈጥሩ ጆሮ የለኝም። እግዚአብሔር በሁሉም ባህል ይከብራል፣ ይከበራል። በሁሉም ቋንቋ ይመለካል። ይሰማል።

የትኛው ቋንቋ ነው ትክክል? የትኛው አጨፋፈር ነው ትክክል? የትኛው አለባበስ ነው ትክክል? ሁሉም ተጠቅልለው የዚህ ዓለም ናቸው። ሐይማኖትም በዚህ ዓለም ይቀራል።

May be a black-and-white image of 1 person and indoor
Advertisement

በፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ

ድሽታ ግና ለመረዳዳት እና ለእርቀ-ሰላም
(መታሰቢያነቱ ለእርቅ ሰባኪው ለፊታውራሪ መኮንን ዶሪ ይሁን!)
++++++++++++++++++
የድሽታ ግና ዕሴቶች በርካታ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ለፈጣሪና ለሰዎች ምስጋና ማቅርብ፣ ያለው ሰው ለለለው ማጋራት ወይም መረዳዳት፣ ተጠራርቶ ፍቅር መግለጽ፣ በይቅርታ እርቀ-ሰላም ማውረድ (ግጭት አፈታት)፣ አብሮነትን ማጠናከር እና ጽዳትና ውበት መጠበቅ ናቸው። የድሽታግና ዕሴቶች የተባሉበት ዋናው ምክንያት በበዓሉ ዋዘማ፣ በበዓሉ ዕለትና በበዓሉ ማግስት በልዩ ትኩረት የሚተገበሩ ስለሆነ ነው እንጂ ዓመቱን ሙሉ የአሪ ህዝብ እነዚህን መልካም ተግባራት ሳይፈጽም ይቆያል ማለት አይደለም።

የዘንድሮው ‘ድሽታ ግና 2015’ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር አስተባባሪነት በድምቀት ሊከበር ዝግጅት መጀመሩንና የበዓሉ መርህ ቃል “ድሽታ ግና ለእርቀ-ሰላም” መሆኑ ተሰምቷል። እኔም በዚህ ጽሑፍ ከስድስቱ አንኳር የድሽታ ግና ዕሴቶች ውስጥ ግጭት አፈታትና መረዳዳት ላይ በማተኮር አጠር ያለ ትንታኔ ለማካፈል ወደድሁ። ይህንን ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት በመጋራትና በባህላዊ ግጭት አፈታት ዙሪያ በአገራችና በዓለም ላይ ያለው አረዳድና አተገባበር ምን እንደሚመስል ለማሳየት ሲሆን አንባቢያን መረጃውን ከአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እያነፃፀሩ ግንዛቤ ያገኛሉ የሚል እምነት አለኝ።

በዛሬው ክፍል አንድ ስለግጭት አፈታት የማቀርብ ሲሆን በክፍል ሁለት የመጋራት/መረዳዳት ባህል መቼና እንዴት ስራ ላይ እንደዋለ፣ በአደጉ አገራት ለምን እንደተሸረሸረና በምን እንደተተካ፣ በታዳጊ አገሮች እንዴት እንደቀጠለ እና ድሽታ ግና የዚህ አብነት መሆኑን እናያለን።

ክፍል 1. ድሽታ ግና እና የግጭት አፈታት

አምና ‘ድሽታ ግና 2014ን’ አስመልክቶ በተዘጋጀው የአሪ ንቓሽ መጽሔት ቁጥር 8 ላይ እንዳሰፈርኩት በአሮጌው ዓመት በተለያየ ምክንያት ተጣልተው ያልታረቁ ወገኖች በድሽታግና የዘመን መለወጫ በዓል ይቅር ተባብለው አዲሱን ዓመት በሰላምና በፍቅር ይጀምራሉ። በአሪ ባህል ፀበኞች ቂም ይዘው ይቅር ሳይባባሉ ማዕድ አብረው አይቆርሱም፣ የደስታ ጊዜ አብረው አያሳልፉም፣ በዓል አብረው አያከብሩም፣ ዘመድ ቢሞት አብረው አልቅሰው አይቀበሩም። ሰዎች ቂምና ቅሬታ እያላቸው በደስታም ይሁን በሃዘን ጊዜ ቢቀላቀሉ ጎሜ ይዟቸው ለከፋ አደጋ ይዳርጋቸዋል ይባላል። ስለዚህ በድሽታ ግና አስገዳጅነት ግጭት አስወግደው በዓሉን አብረው እንዲያከብሩ ይደረጋል።

አተገባበሩ በጊዜና በቦታ ይለያያል እንጂ ባህላዊ ግጭት አፈታት በሁሉም ማህበረሰቦች ወስጥ ይገኛል። በዚህ ጉዳይ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ሰፊ ምርምር ስለተደረገ የጠለቀ ግንዛቤ ተፈጥሯል ማለት ይቻላል። በ2004 ዓም እና በ2005 ዓም “ባህላዊ የግጭት መፍቻ ስርዓቶች በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ በሳተምናቸው ሁለት መጽሐፎች የአገር በቀል ግጭት አፈታት ስርዓቶችን ዓይነት፣ አተገባበር፣ ተቀባይነትና አገልግሎት በዝርዝር አሳይተናል (ገብሬ፣ ፈቃደ እና አሰፋ 2004፣ 2005)። ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ትንተና በ2006 ዓም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ህግ መጽሔት ላይ ካሳተምኩትና ብዙዎች ካነበቡት ስራ ተቀንጭቦ የተተርጎመ ሲሆን ሙሉውን ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ከመጽሔቱ ያገኛሉ (Gebre 2014)።

የግጭት አፈታት መንገዶች ሁለት ሲሆኑ እነሱንም መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ብሎ መለየት ይቻላል። መደበኛው የመንገስት ፍትህ ስርዓቱንና በመንግስት የተቋቋሙ ሌሎች ስርዓቶችን ያካትታል። መደበኛ ያልሆኑት በጣም የተለየዩ ናቸው። በአደጉት የምዕራባዊያን አገሮች በስፋት የሚታወቀውና በታዳጊ አገሮችም እየተለመደ የመጣው አማራጭ የግጭት አፈታት (alternative dispute resolution, ADR) የሚባል ሲሆን ሸምጋዮችና ወይም ገላጋዮች ያሉት ህጋዊ ሰውነት ያለው የግል ተቋም ነው።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በታዳጊ አገሮች መደበኛ ያልሆኑ የግጭት አወጋገድ ዘዴዎች የሚባሉት ባህላዊ ህጎች፣ ሃይማኖታዊ ህጎች፣ የሽምግልናና የግልግል ዳኝነት የሚሰጡ ህጋዊ ድርጅቶች እና መንፈሳዊ ኃይል አላቸው ተብለው የምታመኑ ግለሰቦች ናቸው። ባህላዊ ህጎች ከሰብአዊ መብት፣ ከስርዓተ-ፆታ መብት፣ ከአናሳ ማህበረሰቦች መብትና ከሌሎች ጉዳዮችም አንፃር ክፍተት እንዳለባቸው ይጠቀሳል። ይሁን እንጂ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ በተለይም በገጠር ነዋሪዎች ዘንድ ከመደበኛው ፍትህ ስርዓት የተሻለ ተቀባይነት እንዳላቸው ጥናቶች ያመለክታሉ (Pankhurst and Getachew 2008; ገብሬ፣ ፈቃደ እና አሰፋ 2004፣ 2005)።

በንፅፅር ሲታይ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ከመደበኛው ፍትህ የተሻለ ነው የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች በርካታ ናቸው። አንደኛ ምክንያት በባህላዊ ዘዴ ግጭት የሚቋጨው የበዳይና የተበዳይ ወገን ተግባብተው የአሸናፊነትና የተሸናፊነት ስሜት እንዳይፈጠር ተደርጎ ስለሆነ ተመልሰው ወደ ግጭት ስለማይገቡ የማህበረሰቡ ሰላም ይረጋገጣል የሚል ነው። ነገር ግን በፍርድ ቤት ግጭት እልባት ሲያገኝ በረቺነትና ተረቺነት ስሜት ፀበኞች ቂም ይዘው ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ ስለሚመለሱ ምናልባት በሐሰት መረጃና ማስረጃ ወይም በሙስና ፍትህ የተዛባ ከሆነ በደል የደረሰበት አካል ወደ በቀል ያመራና የማህበረሰብ ሰላም እንደገና ይናጋል።

ባህላዊ የግጭት አፈታትን የተሻለ የሚያደርገው ሌላው ምክንያት በሐቅ የሚመራ በመሆኑ ጥፋት ሰርቶ የሚያመልጥና ያለጥፈቱ የሚቀጣ ባለመኖሩ ነው። ፖሊስና ፍርድ ቤት ማስረጃ በለለበት በምስጢር የተፈጸሙ ጥፋቶችን ለማረጋገጥ ከተቸገሩ ጥፋተኞች በነጻ ሊለቀቁ ይችላል። ጠበቃ ማስተባበል ካልቻለ በሐሰት የተቀነባበረ መረጃና ማስረጃ ተመርምሮ የተዛባ ፍርድ ሊሰጥ ይችላል። ፍትህ መዛባቱን ምናልባት ፍርድ ቤቱ ባይገነዘብም ተበዳይ ስለማይረሳ ለበቀል አመቺ ጊዜ መጠበቁ አይቀርም።

ነገር ግን ጉዳዮች በባህላዊ የግጭት አፈታት ከተያዙ ጥፋተኛን ለመለየት አያስቸግርም ምክንያቱም በማህበራዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ጫና ተጠርጣሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እውነት እንዲያወጡ ይደረጋል፣ ምስክሮችም በእውነት እንጂ በሐሰት እንዳይመሰክሩ ተመሳሳይ ጫና ይደረግባቸዋል። ነገ አብረው ሰለሚኖሩና የእርቁ ዓላማም ቂም በቀል አስወግዶ በሰፈሩ ሰላም መፍጠር ስለሆነ ሐቁ የግድ ይወጣል፤ ፍርድም አይዛባም።

ግልጽነቱና አሳታፊነቱ ሌላው ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴን ተመራጭ የሚያደርግ እንደሆነ ይገለጻል። በአብዛኛው የዕርቅ ስርዓቶች የሚከናወኑት በአደባባይ ሲሆን ከባለጉዳዮቹ፣ ከአስታራቂዎቹና ከምስክሮች በተጨማሪ በታዛቢነት በርካታ ሰፈርተኞች ይገኛሉ። አንዳንዴ ታዛቢዎች የምስክርነት ቃልና የፍርድ አስተያየት ይሰጣሉ። የታዛቢዎች መረጃና አስተያየት እንደህዝብ አቋም ስለምታዩ መግባባት ላይ ለመድረስ ይረዳሉ። የባህል ዳኞች የማህበረሰቡ ታዛቢዎች በተገኙበት ውሳኔ ስለሚያሳልፉ በአድልዎና በሙስና ፍትህ ማዛባት አይችሉም።

ባህላዊ የግጭት አፈታትን የተሻለ ተደርጎ የሚወሰድበት ሌላው ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ የቡድን ግጭቶችን መፍታት መቻሉ ነው። በጎሳዎች፣ በብሔረሰቦች፣ በሃይማኖት ተከታዮች ወይም በሌላ የቡድን ዓይነቶች መሃል ግጭት ተከስቶ ጉዳት ሲደርስ መደበኛው የፍትህ ስርዓት ጥፋተኛውን ቡድን ለይቶ ለመቅጣት ይቸገራል። ቡድኖችን እንዳለ ለፍርድ ማቅረብ ስለማይቻል ከፊት ሆነው ግጭቱን ቀስቅሰዋል፣ አደራጅተዋል ወይም መርተዋል የሚባሉ ግለሰቦች ላይ ብቻ ትኩረት ይደረጋል። ግለሰቦች ብቻ ተፈርዶባቸው ለግጭቱ ምክንያት የሆነው መሰረታዊ ችግር ካልተፈታ ግጭት እንደገና ሊያገረሽ ይችላል። የቡድን ግጭት በባህላዊ የአፈታት ዘዴ ሲያዝ ግን ትኩረት የሚደረገው ግለሰቦች ላይ ሳይሆን ቡድኖች ላይ ስለሆነና የግጭቱ መንስዔ ተለይቶ ስለምፈታ ሰላም ይፈጠራል።

ቅልጥፍናው፣ አምቺነቱና ወጪ ቀናሽ መሆኑም እንደዚሁ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓትን ተመራጭ ያደርጋል። በመደበኛ ፍርድ ቤት ወራት ወይም ዓመታት ሊፈጅ የሚችል ጉዳይ በባህላዊ ዳኝነት በቀናት ወይም በሳምንታት ይቋጫል። ወረዳ ፍርድ ቤት ሲከድ የዳኝነት፣ የጠበቃ፣ የትራንስፖርት፣ የምግብ እና የመኝታ ወጪ ሊኖር ይችላል። የባህላዊ ዳኝነት ችሎት በሰፈር ደረጃ ስለሆነና ጠበቃ ማቆም ስለማያስፈልግ ወጪ የለውም። የወረዳው ፍርድ ቤት ችሎት የሚካሄደው በአማርኛ ከሆነ ቋንቋውን የማይችሉ ባለጉዳዮችና ምስክሮች ሃሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ የማስረዳት ችግር ይኖራል። ዳኝነት በሰፈር ሲሆን ግን የቋንቋ ችግር አይነሳም።

በአጠቃላይ ባህላዊ ግጭት አፈታት ሰላምና ፍትህ ከማስፈን አንፃር ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ህብረተሰቡ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የዘርፉ ተመራማሪዎች ያምናሉ። በባህላዊ መንገድ በየሰፈሩ በእርቅ የሚፈቱ ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት ከሚሄዱ ጉዳዮች በብዙ እጥፍ እንደሚበልጡ ጥናቶች ያሳያሉ። ሁሉም ጉዳይ ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት ቢሄድ ዳኞችና ዐቃቤ-ሕጎች እጅግ የበዛ የስራ ጫና ይገጥማቸዋል ተብሎ ይታመናል።

ከላይ እንደተገለጸው የቡድን ግጭቶችን በመደበኛው ስርዓት መዳኘት አስቸጋሪ ስለሆነ የፌዴራልና የክልል መንግስት ባለስልጣናት ባህላዊ መሪዎችንና የአገር ሽማግሌዎችን ለእርቅ ሲፈልጉ ይስተዋላል። በደቡብ ኦሞ ዞን ቆላማ ወረዳዎች በብሔረሰቦች መሃል ግጭት ሲፈጠር ባለስልጣናት ተሯሩጠው በባህላዊ መሪዎችና በታዋቂ በሽማግሌዎች እንዲፈቱ ያደርጋሉ። በደቡብ አሪና በዎባ አሪ ወረዳዎች ድንበር አካባቢ ተከስቶ የነበረው ግጭት በቅርብ የተፈታው በባለስልጣናት፣ በባቢዎች (የባህል መሪዎች) እና በአገር ሽማግሌዎች ጥምር ጥረት ነው።

ከዚህ ሁሉ የምንረዳው የድሽታ ግና ዓይነት እርቀ-ሰላም ውጤታማ የግጭት መቋጫ መሆኑን ነው። በአሪ ብሔረሰብ በተለያየ ጊዜ ግጭት ለመፍታት ሽምግልና ሲጠራም ይሁን ድሽታ ግና ደርሶ እርቀ-ሰላም ሲወርድ የአሸናፊነትና የተሸናፊነት ስሜት እንዳይኖር በማድረግ የማህበረሰብ ሰላም ይረጋገጣል፣ እውነትን በማውጣት ፍትህ እንዳይጓደል ይደረጋል፣ የእርቅ ሂደትን ግልጽና አሳታፊ በማድርግ ተአማኒነቱ ይረጋገጣል፣ የቡድን ግጭቶች መንስዔው ላይ በማተኮር ዘላቂ መፍትሔ ይፈለጋል እንዲሁም ወጪ የለለበትና የተቀላጠፈ ዳኝነት ይሰጣል። የመደበኛውን ፍትህ ስርዓት መጠቀም እንደተጠበቀ ሆኖ የባህላዊ ዳኝነት ህጋዊነት በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 34 ንዑስ አንቀጽ 5 የተደነገገ ስለሆነ የድሽታ ግናን የእርቅ ዕሳቤ እንደ አማራጭ የግጭት መፍቻ መጠቀም የባለጉዳዮች ምርጫ ይሆናል።
ሰላም ለአገራችን
መልካም ድሽታ ግና

ዋቢ ጽሑፎች
ገብሬ ይንቲሶ፣ ፈቃደ አዘዘ እና አሰፋ ፍስሃ፣ 2004፣ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ስርዓቶች በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ በኢትዮጵያ የግልግል ዳኝነት የማስማማትና ዕርቅ ማዕከል የታተመ መጽሐፍ።
ገብሬ ይንቲሶ፣ ፈቃደ አዘዘ እና አሰፋ ፍስሃ፣ 2005፣ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ስርዓቶች በኢትዮጵያ: ቅጽ 2፣ አዲስ አበባ፣ በኢትዮጵያ የግልግል ዳኝነት የማስማማትና ዕርቅ ማዕከል የታተመ መጽሐፍ።
Gbre Yntiso. 2014. Systematizing Knowledge about Customary Laws in Ethiopia. Journal of Ethiopian Law, 26(2): 28-54.
Pankhurst, Alula and Getachew Assefa (eds.). 2008. Grass-roots Justice in Ethiopia: The Contribution of Customary Dispute Resolution. Addis Ababa: French Center of Ethiopian Studies.

Pagoda Technology Institute

የፖጎዳ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ መስራችና ባለቤት ነው። በቅጽል ስሙ ፖጎዳ እየተባለ ይጠራል። አበራ አልቅሻ ሐሽታ። ተወልዶ ያደገው በደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ዞምባ ቀበሌ ቃናሞር ልማት ቡድን ነው።
ከአንድ እናትና አባት ባንወለድም ከህፃንነት ጀምሮ የምንተዋወቅ አብሮኝ ያደገ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ( ከ1989 እስከ 2000ዓ.ም) አብሮኝ የተማረ ጓደኛዬ ብቻም ሣይሆን ታላቅና ታናሽ ወንድሜም ነው። ከልጅነት እስካሁን በቅርበት አውቀዋለው።
አበራ ከልጅነቱ ጀምሮ ከመጽሐፍ ቅዱስና መደበኛ ትምህርቱ ውጭ ሌላ ምንም የማያውቅ ፍፁም ቅንና ተጫዋች ትውልድ ነው። በቅንነቱ ብዛት በጥጃ እየተመሠለ በቤትና በአከባቢው ኦቲ እየተባለ ይጠራል። ኦቲ በአሪኛ ኦታ የምለውን በማቆላመጥ ስጠራ ሲሆን በአማርኛው ጥጃ የምለውን ስያሜ ያመላክታል ።
ይሁን እንጂ አበራ ከ1ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ስንማር በውጤትም ሆነ በደረጃ የምስተካከለው አልነበረም።
በ1998ዓ.ም በዋልታ ኢንፎርሜሽን ቀርቦ በጠቅላላ ዕውቀት ከሀገር አቀፍ ተማሪዎች ሁለተኛ ደረጃ ወጥቶ ተሸልሟል።
ከ2001 እስከ 2004ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነበረው ትምህርትም ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቦ ተመርቋል።
በነገራችን ላይ አበራ አልቅሻ ይህንን ሁሉ መንገድ ስጓዝ ያለወላጅ አባት ነው። አባትየው ወንጌላዊ አልቅሻ ሐሽታ ገና በህፃንነቱ ለወንጌል አገልግሎት ወደ በረሃ በወጣው በድንገት ባጋጠመው ህመም ሞቶ ያለአባት ነው ደካማ እናቱ ብቻዋን ያሳደገችው ።
ከተመረቀ በኋላ ለአራት ዓመታት በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በብቃት አገልግሏል።
በ2010 ዓ.ም ከክልሉ ቴክንክና ሙያ ቢሮ ባገኘው ዕውቅና ላለፉት ተከታታይ ዓመታት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አራት በዲፕሎማ በማስመረቅ ለዞኑ መንግስትና ህዝብ የማይናቅ ውለታ ውሏል።
ከዚህ አልፎ በሌሎች የዓለም ሀገራት ከቤት ቁሳቁስና ህንፃ መሳሪያነት አልፎ ለምግብነት ጭምር የምውል በኛ ሀገር ብሎም እንደዞናችን ከፍተኛ ምርት እያለን ግን ከአጥርና መሠል አገልግሎት ያለፈ ጥቅም ላይ ስናውል የማይታወቀውን የቀርካሃ ምርት በዘመናዊ መንገድ ለቤትና ለቢሮ መገልገያና ገጣገጥን በማዘጋጀት ምርቱን እያስተዋወቀ ይገኛል።
አበራ አልቅሻ የደቡብ ኦሞ ህዝብ ልጁን በግል ኮሌጆች በአነስተኛ ወጭ በቅርበት እንዲያስተምር ሚቹ ሁኔታ በመፍጠርና የስራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ ከተኮላ ከተማ ቀጥሎ ታርክ የማይረሳው ባለውለታችን ነው።

To be continued . . . .

ወጣትና ነገ

ወጣትነትን ብዙ ሰዎች በዕድሜ ገደብ ብቻ ይተረጉሙታል። ወጣትነትን ከስሜትና ከጉልበት አንጻርም ያገናኙታል። ለኔ ግን ወጣትነት ነገ ነው። አሁን ላይ ነገን የሚያይ፣ ለነገ የሚያስብ፣ ለነገ የሚሰራ፣ ለነገ የሚተጋ፣ ለነገው የሚዋጋ፣ ለነገው የሚሰዋ ነው። ነገ በህይወቱ የለለው ሽማግሌ ነው። ተስፋ የለለው ዛሬን ካደርኩ እግዚአብሔር ይመስገን፣ ለነገ እግዚአብሔር ያውቃል፣ ሰጽንክ ሰካ ዱክተረ አይነት የጨለመ ነብስ የሽማግሌ ነው።

ምን እያልኩ ነው?

ዛሬ ላይ ቆማችሁ ለነገ ምን ያህል ዋጋ ትከፍላላችሁ? ወጣትነት በውስጣችሁ አለ? ነገ ይታያችኋል? ነገን ዛሬ መስራት ጀምራችኋል? ስትማር፣ ስትሰራ፣ ስታቅድ፣ ስታልም፣ ስታሰላስል ነገን ከሆነ ለዚያ የሚያስከፍለውን ዋጋ ክፈል። ለዚያ ራዕይ እስከ መሰዋት ተንቀሳቀስ። ደራሽ በሆኑ ነገሮች መጓዝ ነገን ያራቁታል።

በፖለቲካው፣ በማህበራዊው፣ በኢኮኖሚው፣ በመንፈሳዊው እና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ስትሰማሩ ነገን ብቻ አስቡ። በተለይ ወጣቶች ሰልጥኑ፣ ተማሩ፣ ሩጡ፣ ተንቀሳቀሱ፣ አቅዱ፣ ታገሉ። አከባቢያችሁ፣ ሀገራችሁ፣ አፍሪካ እንዲሁም ዓለም እናንተን ትጠብቃለች። አሁን እኛ ያለንበት ወቅት የትላንት ውጠት ነው። ነገ ላለው ትውልድ የኛ ዛሬ ወሳኝ ነው። ዛሬ ባለህ አቅም ሁሉ ከሰራህ የነገው ትውልድ የተሻለውን ይኖራል

ሸኬን ሸናካን ዳምደክ
ወጣት ለነገው ይዋጋል

ውጊያው በእውቀትና በጥበብ ነው። ከአፈ-ሙዝ በሚሻል ስልት ነው።

ዛቤ

የኣሪ ሕዝብ የመዋቅር ጥያቄ

ደቡብ ኦሞ በ10 ወረዳዎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረች ሲሆን ከነዚያ ውስጥ 4 ወረዳዎች (ሰሜን አሪ፣ ዎባ አሪ፣ ደቡብ አሪና ባካ ዳውላ አሪ) እና ጂንካ ከተማ አስተዳደር በአሪዎች የተመሰረቱ ናቸው። ቀሪዎቹ 5 ወረዳዎች አርብቶ አደር አከባቢዎች የሚገኙበት ነው። ደቡብ ኦሞ በ27 አመቱ የኢህአዴግ አመራር የልማት ኮሪደር እየተባለ በስሙ ስደለል የቆዬ የተበደለ ዞን ነው።

ይሁንና ደቡብ ኦሞ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄው በዞኑ ምክር ቤት ተወስኖ በክልሉ መንግስት ይሁንታ ሳይገኝ የፌደሬሽን ምክር ቤትም ጉዳዩን ባላየ አልፏል። በቅርብ ጊዜ የአሪ ህዝብ በዞን መዋቅር ለመደራጀት በየምክር ቤቶቻቸው አጽድቀው ወደ ዞን ሪፖርት አድርገዋል። የህዝቡን ጥያቄ ከቁብ ያልቆጠረው ደቡብ ኦሞ ምክር ቤቱን ህገወጥ፣ ኢ-መደበኛ እና ሌሎችም አላስፈላጊ ምላሾችን እያንጸባረቀ ነው። ለመሆኑ የአሪ ህዝብ ለምን በዞን መደራጀት ፈለገ?

ጥቅት መሰረታዊ መነሻዎች

  1. ለዞን መዋቅር የሚያስፈልገውን መስፈርቶ አሟልቶ ስለሚያልፍ። የአሪ ህዝብ አሁን ባለው የስነህዝብ መረጃ ከ500,000 አልፏል። ከሀላባ፣ ከኮንሶ በህዝብ ብዛት ይበልጣል።
  2. በደቡብ ኦሞ ዞን ስር ሆኖ ባህሉንና ቋንቋውን ማሳደግ ባለመቻሉ። የአሪ ህዝብ ባህሉን ቋንቋውን በነጻነት ማሳደግ እንዳይችል በደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ አፈና እየተደረገበት ነው። በገዛ ርስቱ የባህሉ መገለጫ የሆኑትን መልበስ፣ ማገጥ፣ መገንባት፣ ማልማት፣ መደራጀት አልቻለም። በዞኑ መንግስት አላስፈላጊ ትርጉም እየተሰጠው ይገኛል። ለአቢነት የአሪ ህዝብ ዘመን መለወጫ በአል “ድሽታ ግና” አራቱም ወረዳዎች በመሰባሰብ በመድናዋ ጂንካ ከተማ ተገኝተው ያከብሩ ነበር። ከበአሉ መገለጫዎች አንዱ የአሪ ባርሢ(ውበትና ገጥ) ነው። ከተማዋን በባህሉ ቀለም አጊጠው እንዳያከብሩ በዞኑ መንግስት ተከለከለ። ይባስም ብሎ ከተማውን ለማገጥ ቀለም ገዝተው ልቀቡ የነበሩ ወጣቶችን ያለ ከሳሽ አስረው ከሳምንት በኋላ ፈቷቸው። ድንጋዮች፣ አደባባዮች፣ ድልድዮች በጸጥታ ኃይል እየተጠበቀ ዋለ አደረ። ይኸ ጫና ባህላችንን በሙላት እንዳናሳይ አንቆናል። ከዚህ በተጨማሪ የአሪ ህዝብ ቋንቋውን የመማር የማስማመር ህገመንግስታዊ መብቱን ዞኑ አደናቅፏል። በጂንካ ከተማ ቋንቋውን እንዳያስተምሩ ተደርጓል። ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ሰብአዊ መብታቸው ነው። ዳሩ ግን ደቡብ ኦሞ ለአሪዎች ያላቸውን ንቀት በዚህ አንጸባርቀዋል።
  3. ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ባለመኖሩ። በደቡብ ኦሞ ዞን በፌደራል መንግስት የሚበጀተውን በጀት አብዛኛው በአሪ ህዝብ ስም ነው። ነገር ግን የተበጀተለት ህዝብ ዞኑ ላይ ስደርስ በስሙ የተመደበለትን በትክክል አያገኝም። ይልቁኑ በዞኑ ውስጥ ላሉት እኩል ይከፈላል። ይኸ በደል ነው።

እነዚህን ለአብነት የጠቀስኳቸው ቢሆንም የደቡብ ኦሞ ዞን አሁንም ቢሆን የአሪ ወረዳ ምክር ቤቶች አጽድቀው የላኩትን በዞን የመደራጀት የመብት ጥያቄ በዝምታ እያየው ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የዞኑ ምክር ቤት ጉዳዩን አይተው አስፈላጊው ህጋዊ ምላሽ ካልሰጡ ፍትህ ለማግኘት ወደ ክልልና ፈደራል መንግስ ፈደረሽን ምክር ቤት ይዘን የምንጓዝ መሆኑ እሙን ነው። የአሪ ዞን ጥያቄ ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ዛሬም ነገም እንጠይቃለን።

We need to be respected

ሕወሓት እና ሴራው

Natnael Asmelash

ህወሓት ከተፈጠረ ጀምሮ ትግራይ የጦር አውድማ ነበረች፣ አሁም ትግራይ
የጦር አውድማ ናት፣ ህወሓት እስካለ ድረስ እስከ ሚቀጥለው ትውልድም የጦር
አውድማ ልትሆን ነው።
ትግራይ ለምን ድሃ ሆነች? ብየ ራሴን ብዙ ጊዜ እየጥይቅ ነበር፣ ትግራይ ድሃ
የሆነችበት ዋናው ምክንያት፣ ትግራይ በትግራይ ተወላጆች ላለፉት አርባ ስድስት
አመታት የጦር አውድማ እንድት ሆን ስለተፈረደባት ብቻ ነው። አባቴ ቤተሰቦቹን
ለማየት ገጠር ሲወስደን፣ የአጎቶቼ እና የአክስቶቼ ኑሮ አይቼ ቡዙ አዘንኩኝ። ያኔ
አያቴ በሁለት በሬ ያርስ ነበር፣ አሁንም ቢሆን አጎቶቼ እና የአጎቴ ልጆች በሁለት
በበሬ ያርሳሉ፣ ትግሉ ውሃ በላው፣ በትግሉ የህወሓት ባለስልጣናት እና
ዘመዶቻቸው ሃብት እና ስልጣን አካበቱበት፣ የትግራይ ህዝብ ግን አሁንም ቢሆን
ከአርባ ስድስት አመታት ቦሃላ አዲስ ጦርነት ከፍተውለት፣ ልጆቹን አስግብረው
ትግራይ የጦር አድውማ አድርገዋታል። ስለዚህ የትግራይን ህዝብ ከዚህ አዙሪት
ወጥቶ እንደ ሌላው ቢሄር ቢሄረሰብ በሰላም እንዲኖር የትግራይ የተቃዋሚ
ፓርቲ አመራሮች ምን እየጠበቃቹ ነው? ያለ መስዋእትነት ድል የለም፣ የህወሓት
ባለስልጣናት ፈርቶ እና አክብሮ የትግራይን ህዝብ ስቃይ እና መከራ እስከ መቼ
ይቀጥል? ባለፉት አርባ ስድስት አመታት ህወሓት ከተፈጠረ ጀምሮ በትግራይ
የተደረጉ ጦርነቶች እንመልከት።


፩ ህወሓት Vs ግገሓት 7/3/1968

(ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ)
ህወሓት ከምሰረታው ጀምሮ በትግራይ እኔ ብቻ ነኝ መንቀሳቀስ ያለብኝ ብሎ
ካጠፋቸው የትግራይ ታጋዮች የግገሓት የነበሩ አመራሮች ናቸው። “ህወሓት
መዋሃሃድ አለብን ብሎ ከግገሓት አመራሮች ጋር ስምምነት ካደረገ ቦሃላ፣ ለሊት
11:30 በተኙበት በግገሓት አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰዱ፣ የዚህ እርምጃ ዋና
ተዋናይ ስዩም መስፍን ነበር። የግገሓት ሰባት ከፍተኛ አመራር የሆኑም ተገደሉ.
1.የማነ ገብረመስቀል፣. 4. ሃይላይ 7. ኪዳነ ደስታ
2.አብርሃ ተሰማ፣. 5.ሓዱሽ ባይነሳይ
3.ባራኺ ገብሩ፣ 6. አፈወርቂ ተፈሪ
ከሞት የተረፉት በካቴና ታስረው እስርቤት ገቡ፣ ከሞት ተርፈው ሓለዋ ወያነ
የገቡ
1.የውሃንስ ተኽለሃይማኖት፣ 3.ተፈራ ካሳ፣
2.ኤፍረም ወዲ ሻለቃ፣ 4.ሃይለሚካኤል ወዲ አባ ጎበዝ ነበሩ፣
ስብሓት ነጋ የሓለዋ ወያነ ዋና ጠባቂ ሆኖ የግገሓት አመራሮች ታሰሩ”።(ምንጭ
ጋህዲ-2 አቶ አስገደ ገብረስላሴ ገፅ 80-83)
“ይህ ሴራ ተግባራዊ ያደርግ ዘንድ እያንዳንዱ የህወሓት ታጋይ እና አመራር፣
ከግገሓት አመራር አንድ ለአንድ አብሮ እንዲተኛ ተደረገ፣ ጎሕ ሊቀድ ሲል
የህወሓት ታጋዮች ምልክት ተሰጣቸው፣ ሁሉም እጃቸው እንዲሰጡ ተጠየቁ፣
እምቢ ያለው ልበ ደንዳናው የማነ ገብረመስቀል ተገደለ፣ (ምንጭ አቶ ገብሩ
አስራት ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጲያ ገፅ 64)
ይህ አሁን ካለው የኢ/ያ ታሪክ ጋር ስናያይዘው፣ ስብሓት ነጋ እና ስዩም መስፍን
በመከላከያ የፈፀሙት ክህደት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፣ መከላከያ በተኛበት
የረሸኑ፣ በባዶ እግሩ እንዲራመድ ያደረጉ ዛሬ ላይ ዋጋቸው ማግኘታቸው
አስደሳች ነው።


፪ ህወሓት Vs ኢድህ 20/06/70
“ህወሓት የኢድህ ሰራዊት ከአድያቦ አከባቢ ካስወጣው ቦሃላ፣ ማይተመን፣ ማይ
ቀይሕ፣ዓዲ ጎሹ በተባሉ አከባቢዎች የኢድህ ሰራዊት በመክበብ በህወሓት
አሸናፊነት ኢድህ ሙሉ ለሙሉ ተሸንፎ ተደምስሶ ከትግራይ እንዲወጣ ተደረገ;
የተረፈ አብዛኛው ወደ ሱዳን ሸሸ”(ምንጭ ጋህዲ-2 አቶ አስገደ ገብረስላሴ ገፅ
156-161)።
ከጦርነቱ በፊት ኢድህ ከትግራይ ህዝብ ለመነጠል ህወሓቶች የትግራይ ህዝብ፣
ትግራይ የምትባል አገር ለመመስረት እንደሚታገሉ፣ ኢድህ ግን ኢትዮጲያውያን
ነን፣ የሚታገሉትም ለኢትዮጲያ ነው ብለው ህዝብን ይሰብኩት ነበር፣ ልክ አሁን
የትግራይን ወጣት ለመፍጀት፣ ትግራይ የምትባል አገር እንመሰርታለን ብለው
ፖለቲካ እንደሚሰሩት ማለት ነው፣ እስከ ደሴ ድረስ እስኪቀናቸው ግን እንጦጦ
እንገባለን ብለው ነበር።

፫ ህወሓት Vs ኢህአፓ 1970-1972
ህወሓት ጠባብ ከመሆኑም በላይ፣ ትግራይ እና የትግራይን ህዝብ የኔ ብቻ ነው
ብሎ ስለሚያስብ፣ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በሙሉ ከትግራይ
እንዲወጡ ይፈልግ ነበር፣ ከነዚህ ድርጅቶች አንዱ ኢህአፓ ነው።
ኢህአፓ ከትግራይ በስተ ደቡብ ባለው የአገራችን አከባቢ እንዲቀሳቀስ እና
ትግራይን ለህወሓት እንዲተው በህወሓት ሓሳብ ቀረበ። በዚህ ጊዜ ኢህአፓ
ከህወሓት ጋር ሳይስማማ ቀረ። ኢህአፓ ዓይጋ በተባለው ስፍራ ህክምና ውስጥ
በነበሩ የህወሓት ታጋዮች ላይ ጥቃት ካደረሰ ቦሃላ፣ የህወሓት ታጋይ እና አመራር
ኢህአፓን በውግያ ማስወገድ ብቸኛው አማራጭ መሆኑን አምኖበት፣ ኢህአፓም
እንደ ሌሎች ፓርቲዎች በውግያ እንዲደመሰስ ወሰነ። ከብዘት በስተ ደቡብ ባሉ
ከፍተኛ ተራሮች ከባድ ውግያ ከተካሄደ ቦሃላ፣ ከሁለቱም ወገኖች ብዙ ሰው
አልቆ ኢህአፓ ተሸንፎ ከትግራይ ጠቅልሎ ወጣ፣ ወዳጁ ከነበረው ጀብሃ ጋርም
ተቀላቀለ፣ ኢህአፓ በጀብሃ ድጋፍ ወደ ወልቃይት ያደረገው ጉዞ ሳይሳካለት
ቀርቶ፣ ህወሓት ኢህአፓን ወልቃይት ድረስ ገብቶ ከወልቃይትም ገፍቶ አወጣው።
(ምንጭ አቶ ገብሩ አስራት ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጲያ ገፅ 73-77)
“በሌላ ገፅ ህወሓት በፕሮግራም ደረጃ ያስቀመጠው እና ተግባራዊ ያደረገው
ነገር ቢኖር ከአማራ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መስራት አይቻልም፣ ከኢህአፓ ሆነም
ከሌሎች ኢትዮጲያውያንም ቢሆን አብሮ መታጋል አይቻልም፣ ህወሓት በሰላማዊ
መንገድ ችግሮችን የመፍታት ፖለቲካዊ ባህል አልነበረውም”።(ምንጭ
ጋህዲ-2 አቶ አስገደ ገብረስላሴ ገፅ 177)
የአዲግራት ዛላንበሳ መንገድ በመያዝ፣ ዕዳጋ ሓሙስ ሰንቃጣ መንገዶችን
በመቁረጥ፣ የኢህአፓ ቦታ ዓንሰባ ማዕሚኖ ሰንገዳ አልፈው ለአምስት ቀናት
በተደረገ ውግያ ህወሓት ቦታውን ተቆጣጠረው፣ ኢህአፓ ተሸንፎ ወደ ኢሮብ
አመራ፣ ህወሓት ተከታታይ ማጥቃት በማድረግ ኢህአፓ ከትግራይ መሬት
ጠቅልሎ እንዲወጣ ካደረገ ቦሃላ፣ ምርጫ ያልነበረው ኢህአፓ ሳይወድ በግድ
ከሚጠላ ጀብሃ ስር በስመጃና አከባቢ ተጠለለ”።(ምንጭ ጋህዲ-2 አቶ አስገደ
ገብረስላሴ ገፅ 181)
ልብ በሉ፣ አብዛኛዎቹ የኢህአፓ አመራሮች የትግራይ ተወላጆች ነበሩ፣ ዶ/ር
ተስፋይ ደበሳይ፣ ዘርኡ ክሕሸን፣ የውሃንስ ክፍሌ፣መስፍን ሓብቱ፣አባዲ አብርሃ፣
(ምንጭ ያ ትውልድ ፣ክፍሉ ታደሰ ቅፅ አንድ ገፅ 62-73)
ህወሓት በትግራይ የሚገኙ ማናቸውም ለውጥ ፈላጊ ፓርቲዎች ጋር ቢሄራቸው
ምን ይሁን ምን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሳያስገባ ሁሉም ነገር በጦርነት ብቻ
እንደሚፈታ ፕሮግራሙ ላይ አስቀምጦ ተግባራዊ አድርጎታል፣ ትግራይ የጦር
አውድማ የሆነች በህወሓት የስልጣን፣ የዴሞክራሲ፣ የፖለቲካ እና የእኔ ብቻ ነው
የማውቅልህ ትእቢት ነው። ከፍተኛ የኢህአፓ አመራሮች የትግራይ ተወላጆች
ቢሆንም እነሱንም ገድሎ ርስት ይመስል ትግራይ የብቻውን አድርጎዋታል።


፬ ህወሓት Vs ጀብሃ 1973
በህወሓት እና በጀብሃ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ዋናው ምክንያቱ ህወሓት
በግገሓት ላይ የወሰደው እርምጃ ነው፣ ጀብሃ ቆይቶም ከኢድዩ(ኢድህ)ጋር
ስምምነት ፈጥሮ ህወሃትን ለማጥፋት በማሰቡ እና ኢህአፓን ከኤርትራ መሬት
ወደ ወልቃይት እና ፀገዴ ለማሸገር ማሰቡ ና ከለላ መስጠቱ ነበር።(ምንጭ
ጋህዲ-2 አቶ አስገደ ገብረስላሴ ገፅ 264)
ህወሓት በኤርትራ ቆላማ እና ደጋማ አከባቢዎች የነበረውን ጀብሃ ጠራርጎ
ለማውጣት እስትራቴጂ ነደፈ፣ በዚህም መሰረት ምእራፍ አንድ እና ሁለት
ተብሎ፣ ምእራፍ አንድ ዘመቻ በደንከል፣ አከለጉዛይ የነበረው የጀብሃ ታጋይ
ጠራርጎ አወጣው፣ ምእራፍ ሁለት፣ ሰራየ፣ ባርካ የነበረው የጀብሃ ታጋይ ጠራርጎ
አወጣው፣ ከሰኔ 30/10/73 እስከ ነሓሴ 30/02/73 በተደረገ ጦርነት ጀብሃ ሙሉ
በሙሉ ከኤርትራ መሬት ጠቅልሎ ወጥቶ የስደት ኑሮም በሱዳን አንድ ብሎ
ጀመረ. (ምንጭ ጋህዲ-2 አቶ አስገደ ገብረስላሴ ገፅ 273)
የጀብሃ ታጋይ በውግያ ልምዱ እና ቆራጥነቱ ባይታማም በሁለት ነገሮች ግን
ለሽንፈት ተዳርገዋል፣ ፩ በውስጡ የነበረ ቀውስ ፪ ህወሓት እና ሻእብያ በጋራ
የፈጠሩት ጊዚያዊ ትብብር. (ምንጭ አቶ ገብሩ አስራት ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ
በኢትዮጲያ ገፅ 103)


፭ ህወሓት Vs ደርግ 1980-81
የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ቄራ ተገኘ እንዲሉ ትግራይን ከወያኔ ነፃ አውጥቶ ወደ
ኤርትራ ይገሰግሳል የተባለው የ 604ኛ ኮር ሸሬ እንዳስላሴ ላይ በሚያሳዝን
ሁኔታ በህወሓት ተደመሰሰ። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ እና በሽሬ ውድቀት ሞራሉ
የላሸቀው ጦር ወያኔ ተከታትሎ በጳጎሜ 1981 የከፈተብን ማጥቃት ብዙም
ሳይቋቋም ወደ ወልድያ አፈገፈገ፣ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ተለቀቀ. (ምንጭ
አብዮቱና ትዝታየ ሌ/ኮ ፍስሃ ደስታ ገፅ 457)
ይህ የተጠናከረ ወታደራዊ አቅሙን በቅድምያ የፈተሸው በ1980 ዓ.ም. ውስጥ
በርካታ ከተሞችን በመቆጣጠር ባሳየው ብቃት ነበር። በውቅቱ ቀድሞ ጭራሽ
የማይታሰበውን በአውራጃ ከተሞች ሰፍሮ የነበረውን ግዙፍ የደርግ ጦር
ማጥቃት ጀመረ፣ ሽሬን አክሱም አድዋን በአንዴ ከደርግ ሰራዊት ለማላቀቅ
ተቻለ። ((ምንጭ አቶ ገብሩ አስራት ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጲያ ገፅ
138)

ህወሓት Vs ህወሓት
Every individual full or deputy CC member of the Tplf had the
power to pass a death sentence without consulting others.
Victims had no right of appeal. As long as they did not expose
the person who ordered the killings on youngsters, all members
of the leadership defend those who committed crimes against
the victims at the cost of justice and democracy.(Ethiopian
democratization and Unity Kahsay Berhe P-55)
They suspected Ghidey Woldegiogis, one of their friends to be
an agent of the regime and started to beat him with sticks and
burn him with hot sticks, without any evidence. (Ethiopian-
democratization and Unity Kahsay Berhe P-10)
Teclu Hawaz, a member of the CC of the Tplf who did not
agree with the measures taken against Aregawi Berhe and
Ghidey Zeratsion, was sent into the battle as the plan to
murder him. Teclu Hawaz killed. (Ethiopian democratization
and Unity Kahsay Berhe P-85)
Why Meles Zenawi was not punished for cowardice according
to the law of Tplf, for not fulfilling his duty during a military
operation in Adwa in 1977 The operation was aborted and a
fighter called Tecle Gebre yohannes was shot and his body left
behind, Such a crime carriers a death penalty in the tplf and it
was often applied. (Ethiopian democratization and Unity
Kahsay Berhe P-54)
There is concrete evidence that members from Adewa, like
Tesfay Hailu(murdered) and Teshome Gudo, who escaped
when Abadi Hailu (from Temben) and Oqubazghi (Rezene)
Beyene (from Axum) lost their lives and Mesfin (from Enderta)
was Arrested. (Ethiopian democratization and Unity Kahsay
Berhe P-290)


፮ ህወሓት Vs ሻእብያ 1991-93
በባድመ በኩል የተከፈተው ጥቃት የሻእብያ ሃይል ሊቋቋመው ባለመቻሉ
የኢትዮጲያ ሰራዊት የሻእብያን ሰራዊት እየተከታተለ እስከ ደጋው የሰራየ ክፍል
ማለትም እስከ ዓረዛና ሌሎች ስታራቴጅያዊ አከባቢዎች ድረስ ዘለቀ፣ በጸሮና
ግምባር ተመሳሳይ ጥቃት ከፍቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሃዞሞን ሜዳ፣ ጸሮና እና
ሌሎች በአቅራብያው የነበሩትን አነስተኛ ከተሞችንም ለመቆጣጠር ቻለ።
(ምንጭ አቶ ገብሩ አስራት ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጲያ ገፅ 312)
የባድመ ጦርነት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ለሁለት እንዲሰነጠቅ አድርጎ
ህወሓት የቁልቁለት መንገዱን እንዲጀምር መንገድ ከፈተ፣ ህወሓቶች ሻእብያን
ለማዳከም ብለው “No War No Peace” የሚል ፖሊሲ መከተል ጀመሩ፣
ዳሩ ግን ይህ ፖሊሲ ሻእብያን አጎልብቶ ህወሓት አዳክሞ፣ የትግራይ ህዝብ
ከልማት እንዲገለል አድርጎ፣ የህወሓት ሞት እና ቀብር አቀላጠፈው። (የግሌ
ሃሳብ ነው)


፯ ህወሓት Vs ብልፅግና እና ሻእብያ 2013
ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ በከፈተው ድንገተኛ ጦርነት፣ ህወሓት የሰሜን እዝ
ወታደሮች ገድሎ ማርኮ በሰሜን እዝ ላይ ክህደት ከፈፀመ ቦሃላ፣ በደቡብ
ምስራቅ እና በምእራብ ኢትዮጲያ ከነበረው የመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት
የሰሜን እዝ ወታደሮች ወደ ኤርትራ በመዝለቅ ተደራጅተው ባደረጉት የፀረ
ማጥቃት ጦርነት፣ የሰሜን እዝ ወታደሮች በደቡብ በራያ በኩል መቀሌ ፣ በሁመራ
ሽሬ ነፃ ባማውጣት፣ ህወሓትን ደመሰሱት፣ በሰሜን በኩል ሁለት ሚሳይል በገዛ
መሬቱ የተወረወረበት የኤርትራ መንግስት፣ ድምበሩን እና አገሩን ስለተደፈረ፣
የዛላምበሳ አድዋ አክሱም በመቆጣጠር ህወሓትን ደመሰሰው፣
ብልፅግና፣ሻእብያ፣የአማራ ፋኖ እና ምሊሻ የኢትዮጲያም የኤርትራም ጠላት
የሆነው ህወሓትን በቅንጅት በመዋጋት ደመሰሱት፣ ትግራይ ከህወሓት ሙሉ
በሙሉ ነፃ ወጣች። የትግራይ ህዝብ በህወሓት ክህደት የተፈፀመበትን የሰሜን
እዝ ሰራዊት ወደ ትግራይ ሲገባ ከህወሓት አመራሮች ጎን ሁኜ መከላከያን
አልወጋም በማለት በደስታ መከላከያን ተቀበለው፣ ህወሓትም እንደለመደው
የትግራይን ህዝብ ለማስፈጀት ተመልሶ ከአርባ አምስት አመት ቦሃላ ደደቢት
ጫቃ የተፈጠረው ህወሓት አብዛኛው አመራሩን አስገድሎ፣ ግማሹ ተማርኮ፣
ግማሹ የሴት ቀሚስ ለብሶ ፣ ቄስ መስሎ ለማለጥ ሲል ተማርኮ በሂወት
የተረፈው የትጥቅ ትግል ለማድረግ ተምቤን ዋሻዎች ገባ። (ምንጭ እኔው ራሴ)

ለትግራይ ህዝብ ጥፋት እንጂ ሰላም እና ልማት የማያመጣው ህወሓት፣
መከላከያ ትግራይ ለቆ ሲወጣ፣ ህወሓት የብልፅግና ደጋፊዎች እና ተላላኪዎች
ናቹ ያላቸውን የትግራይ ተወላጆች፣ በትግራይ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ፣ ህዝቡም
ይማር ብሎ ብዙዎችን ገደለ አሰረ፣ የትግራይ ህዝብ A,B,C,D ብሎ በአራት
ከፋፍሎ፣ በትግራይ ጭቆናው ቀጠለ፣ አራት ኪሎ የሚናፍቀው ህወሓት ሚስኪኑ
የትግራይ ወጣት ደብረብርሃን ድረስ እንዲዋጋ አድርጎ፣ ተመልሶ መቀሌ ገብቶ
ብዙ የትግራይ ወጣቶችን አስፈጀ፣ የትግራይ ህዝብ ልጆቼ የት ገቡ ብሎ
እንዳይጠይቅ፣ መፍትሄው ጦርነት ብቻ ነው ሲል የነበረው ህወሓት፣ የሰላም
ድርድር ጠበቃ ሆኖ፣ ያለ ሳአቱ እና ቀኑ፣ የሰማእታት ቀን ብሎ በማወጅ፣
የትግራይ እናቶች ከተምቤን እስከ ደብረብርሃን፣ ከደብረብርሃን እስከ ራያ
ድምበር ላይ ያለቀውን የትግራይ ትውልድ እንዳይጠይቅ ሰኔ ወር ሲከበር
የነበረው የሰማእታት ቀን ድንገት ታህሳስ ላይ እንዲከበረ አደረገ። ህወሓት
ከተፈጠረ ጀምሮ የትግራይ ህዝብ በሰላም የኖረባቸው አመታት አስር አመት ብቻ
ናቸው። https://www.youtube.com/watch?v=TMtJMbX1
0aE&t=1158s
ለብሄር ቢሄረሰቦች ዴሞክራሲ አመጣሎህ ብሎ የሚጮሆው ህወሓት፣ ትግራይ
ውስጥ የሚገኙ የህወሓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሚዲያ በመከልከል፣ የተለየ
ሃሳብ ላቀረቡ እነ ማሓሪ የውሃንስ እና ኪዳነ አመነ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣
በዚህ የተደናገጠው የህወሓት ጀነራል ተሰብስቦ መግለጫ በመስጠት ባሁኑ
ሳአት ክፍተት የሚፈጥር ትግራዋይ የብልፅግና እና የሻእብያ ተላላኪ መሆኑን
በግልፅ በሚዲያቸው ተሰባስበው ገለፁ፣ ህወሓት እንደ መልአክት ታቦት
ሊሰራበት የሚገባ ፓርቲ ነው ብለው፣ አዲሱን የትግራይ ትውልድ እነሱ ካሉት
ውጭ ምንም አይነት ፖለቲካዊ ጥያቄ እንዳያቀርብ አራት ነጥብ አረጉበት።
ትግራይ ያሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚዲያ ሙሉ በሙሉ ተከለከሉ፣ የትግራይ
ዳያስፖራ ትግራይ ውስጥ ላሉት የባይቶና፣ሳወት እና ውናት ጠበቃ ለመሆን ፈሩ፣
ባርነታቸው ለህወሓት አመራሮች አስመሰከሩ።
ህወሓት በዲፕሎማሲም በፖለቲካም ተሸነፈ፣ የትግራይ ዳያስፖራ ጠበቃ
ይሆነናል ያሉት ጆባይደን፣ ኢትዮጲያውያን በሚቀጥለው ምርጫ ለሪፓፕሊካን
ይመርጣሉ በሚል ከኢትዮጲያ ጎን ሳይወድ በውዱ ተሰለፈ። የትግራይ ህዝብ
በገዛ ልጆቹ የህውሓት ጀነራሎች እና አመራሮች በታሪኩ አይቶት የማያቀውን
ውርደት፣ ስደት ርሃብ እና መከራ ደረሰበት።የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሃሳባቹ
በነፃነት እንዳትገልፁ፣ ህዝብ እንዳታደራጁ ያደረጋቹ ህወሓት ነው ጠላታቹ
ወይንስ መንግስት? https://www.youtube.com/watch?v=MEg1lB6g
7Fo&t=1696s
የትግራይ ወጣት፣ የትግራይ ትውድል፣ የትግራይ ሙሁር፣ የትግራይ ዳያስፖራ
ሆይ! የትግራይ ህዝብ ህወሓት ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አርባ ስድስት አመት
ሆኖታል፣ የትግራይ ህዝብ ግን ህወሓት ከተፈጠረ ጀምሮ ለአርባ አመታት
በጦርነት እንዲኖር ተደርገዋል፣ ሁለት መቶ ሺ ልጆቹን የገበረው የትግራይ
ህዝብ፣ በልጆቹ ደም እና አጥንት ስልጣን የያዙ የህወሓት አመራሮች፣ ለሃያ
ሰባት አመታት ያክል ረስተውት፣ ዳግም ከአማራው፣ አፋር፣ ከኤርትራው እና
ከመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ጋር ደም አቃብተው ጠላት ፈጥረውለት; እንሆነ አንድ
አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከመቶ ሺ በላይ የትግራይ ወጣት ትውልድ
እንዲረግፍ አድርገዋል፣
አሁንስ የትግራይ ህዝብ ጠላት ማን ይሆን? ተከዜ ተሻግሮ ያለው ብልፅግና
ወይንስ መረብ ወንዝ ተሻግሮ ያለው የኤርትራ መንግስት! የትግራይ ትውልድ፣
ለስልጣናቸው የሚኖሩ፣ ለሃብታቸው የትግራይን ወጣት ወደ ጦርነት የሚማግዱ
የህወሓት ባለስልጣናትን ታግለህ እና ደምስሰህ፣ አዲስትዋ ትግራይ
እስካልመሰረትክ ድረስ የትግራይ ህዝብ ፣ ተረፈ ምርት በሆኑ የህወሓት
አመራሮች እስከተመራ ድረስ እጣችን ሞት፣ስደት እና መከራ ብቻ ነው! ያለን
አማራጭ ህወሓት ቀብረን፣ ትግራይ በአዲስ ትውልድ መርተን፣ ከመላው
የኢትዮጲያ እና የኤርትራ ህዝብ ጋር በሰላም፣ በፍቅር፣ በመቻቻል መኖር ብቻ
ነው! https://www.youtube.com/watch?v=PfmYJuBC
Hec&t=2419s
እንግዲህ ህወሓት ከተፈጠረ ጀምሮ ትግራይዋይ እና ትግራይ; ከትግራይ
ተወላጆች፣ ከኤርትራ ተወላጆች፣ ከኢትዮጲያ ተወላጆች ጋር በደም እንድትቃባ
ተደርገዋል፣ በቅርቡ ህወሓቶች የትግራይን ህዝብ ከሁሉም ቢሄር ቢሄረሰቦች
በተለይ ደግሞ፣ የትግራይን ህዝብ ጎረቤት ከሆነው አማራው፣አፋሩ እና
ኤርትራዊው ጋር ደም አቃብተውታል፣ አሁንስ ህወሓቶች ወደ ስልጣን እስኪመጡ
ድረስ ስንት የትግራይ ወጣት ይለቅ? ትግራይ እስከ መቼ ነው የጦር አውድማ
የምት ሆነው? ህወሓት እንደምስስ ወይስ በህወሓት ምክንያት የትግራይ ህዝብ
ልጆቹን ይገብር? አሁንም የትግራይ ትወልድ ጥያቄው ላንተ ሆኖ መልሱ ደግሞ
እጅህ ላይ አለ። ምርጫው አንድ ነው።ህወሓት ከነአካቴው ይጥፋ ወይንስ
የትግራይ ህዝብ ይጥፋ!! ይህ ጦርነትስ መች ያበቃ ይሆን? አሁንም ድል
ለትግራይ ህዝብ ሞት ለተረፈ ምርት የህወሓት አመራሮች።
N.B. የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሆይ፣ የትግራይ ዳያስፖራ በትግራይ
ፍትህ፣ሰላም፣ ፖለቲካዊ እና ዴሞክራስያዊ ለውጦች እንዲመጡ፣ በህወሓት
ላይ ግፊት ያደርጋል ብላቹ እንዳታስቡ፣ በትግራይ ዳያስፖራ በተማረውም
ባልተማረው ተስፋ አታድርጉ፣ የትግራይ ዳያስፖራ እና ሙሁር ለህወሓት ባርነቱ
አምኖ ተቀብሎታል፣ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀውን ወገንተኝነት ለትግራይ
ህዝብ ሳይሆን፣ ለህወሓት አመራሮች እና ጀነራሎች አሳይተዋል፣ የትግራይ
ዳያስፖራ እና ሙሁር ስለ ትግራይ ህዝብ የማይጨነቅ ጨካኝ የህብረተሰባችን
ክፍል ሆኖዋል፣ ስለሆነም ራሳቹ በትግራይ ውስጥ የሚገኝ ወጣት እና
የትግራይን ሰራዊት አደራጅታቹ ለውጥ ለማምጣት ለመጣር ሞክሩ፣ ድንገት
ህወሓት እንደ ግገሓት ታጋዮች ከገደላቹ እና ካስገደላቹ ታሪካቹን እንፅፈዋለን
እንተርከዋለን፣ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ሆነ እንጂ ህወሓት እናንተን እንደ
ግገሓት አመራሮች፣ እንደ ሰሜን እዝ ወታደሮች ለመግደል ካሰበ ቆይተዋል፣
ከትግራይ ህዝብ ጋር ለሚደርሰው ፖለቲካዊ ተቃውሞ ስለሚያውቀው ግን
አላደረገውም፣ ስለሆነም የትግራይን ህዝብ ተማምናቹ የትግራይ ህዝብ ከዚህ
ሁሉ ችግር እና መከራ እንዲወጣ ታሪካዊ ግዴታቹ ትወጡ ዘንድ መልእክቴን
አስተላልፋለሁኝ፣ በምታደርጉት ትግልም ከጎናቹ ነኝ። ለጀነራል ሓየሎ አርአያ
ያልሆነ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ሊሆን አይችልም!!!
ግልባጭ ከትግራይ ህዝብ ይልቅ፣ ለህወሓት ጀነራሎች እና አመራሮች
ባርያነትክን ላስመሰከርከው የትግራይ ሙሁር እና የትግራይ ዳያስፖራ!!!
ናትናኤል አስመላሽ
01/14/2022
አሜሪካ

ከሙሴ ወንበር ወደ ፍቅር ዙፋን

” ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።”
(የማቴዎስ ወንጌል 23:2)

ብዙ የዘመናችን አገልጋዮች፡ የቤተክርስቲያን መሪዎች እንደ ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር የተቀመጡ ናቸው፡፡ የሙሴ ወንበር ማለት የሰዎችን ሐጢአት እየቆጠረ ፍርድ የምሰጥ ነው፡፡ ክዳን እንደተቀየረ፡ በክርስቶስ የሐጢአት እዳ እንደተከፈለ፡ ከሥራ ጽድቅ ወደ እምነት ጽድቅ እንደተቀየርን፡ ሥራ ሁሉ በክርስቶስ ማለቁ(መፈፀሙ)፡ ሕጉ መወገዱ፡ ከሳሽ መጣሉ፡ አሮገው መወገዱ ያልገባቸውና መቀበል የቸገራቸው ዛሬም ድረስ ያንን የሞት አገልግሎት የምያደርጉ ናቸው፡፡

” ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ #ስለ_ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ #የሞት_አገልግሎት በክብር ከሆነ፥”
(2ኛ ቆሮንቶስ 3:7)
የሙሴ አገልግሎት መገለጫ ከሆኑት ነገሮች አንዱ የካህናት አገልግሎት ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ካህናት የሰዎችን ሐጢአት ሰምተው መስዋዕት የምያደርጉ ናቸው፡፡ የትኛውም ሰው በየአመቱ በግ ይዞ በካህኑ ፍት ይናዘዛል፡፡ ይኸንን እስካላደረገ ድረስ ምንም አይነት ጊዜያዊ ፈውስ አያገኝም ነበር፡፡

የተወደድክ! ዛሬ ሐጢአትህን በፍታቸው ቀርበህ እስካልተናዘዝክ ድረስ የማይቀበሉህ ሰዎች አልገጠሙህም? የሙሴን ጥቅስ እየወሰዱ የሰውን ጉድ ለመስማት አሸንክታባቸውን ያሰፉ ሰዎች አላየህም? አስተውለህ ካየሃቸው ስብከታቸው፡ ንግግራቸው፡ ፀሎታቸው ሁሉ ሕግ ነው፡፡ የተፈፀመውን የቤዛ አገልግሎት ማገልገል አይችሉም፡፡ የሚቀናቸው አመንዝራለች ትወገር ነው፡፡ ውጫዊ ነገር ላይ ማተኮር ነው፡፡ የሐይማኖትን ሸክም ማሸከም ነው፡፡

” ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።”
(የማቴዎስ ወንጌል 23:4)

ወዳጄ! ልትጸድቅበት የማትችለውን ሥራ ይነግሩሃል፡፡ አንድ ነገር ልንገርህ! ጽድቅ በማመን ብቻ ይገኛል፡፡ ይኸንን እውነት ከቃሉ ታገኛለህ፡፡ የእምነት ጽድቅ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሲሆን የሕግ ጽድቅ ግን የመርገም ጨርቅ ነው፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ እንዲህ ያለው፡-

” እላችኋለሁና። ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።”
(የማቴዎስ ወንጌል 5:20)

አየህ? የእግዚአብሔር መንግሥት የምገባው ልጁን በማመን ነው፡፡ ልጁን ማመን ደግሞ በልጁ የእግዚአብሔር ጽድቅ መሆን ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆንክ ማለት ደግሞ ከፈሪሳዊያንና ከጻፎች ጽድቅ መብለጥ ነው፡፡ በሙሴ ሕግ መጽደቅ አይቻልም፡፡

” እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።”
(የሐዋርያት ሥራ 13:38-39)

እናም ወዳጄ! በሙሴ ወንበር የተቀመጡ የዘመናችን ፈሪሳውያን ጸድቀያለሁ ስትል የምናደዱት ይኸ ምሥጢር ስላልገባቸው ነው፡፡ አሁንም የጽድቅ ሥራ እንዳለ ባለማመን በሕጉ ሥራ ላይ ታስረዋል፡፡ በሕግ ሥራ ለመጽደቅ መሞከር ትርፉ ውድቀት ነው፡፡

” በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።”
(ገላትያ 5:4)

በክርስቶስ ኢየሱስ አምነሃል? መልስህ “አዎ” ከሆነ እንኳን ደስ አለህ፡፡ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተደርገሃል፡፡
☞ በክርስቶስ ያላመንክ ወዳጄ! ዘመንህን የሐይማኖትን ሸክም እየተሸከምክ ራስህን አትኮንን፡፡ ቶሎ ብለህ ወደ ክርስቶስ ቅረብ፡፡ እሱን በማመን የእግዚአብሔር መንግሥት ተካፋይ ሁን፡፡ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሁን፡፡ ሸክምን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣል፡፡

” እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።”
(የማቴዎስ ወንጌል 11:28)

አየህ ወዳጄ! እረፍት ያለው በክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ሸክምህን በእርሱ ጣልና በነጻነት ያለ ኩነኔ መኖር ጀምር፡፡

Ager Mountain

NoMore western democracy!

“ለሽብርተኞች ምህረት ማድረግ የፈጣሪ ሥራ ነው፤ የእኔ ሥራ እነሱን ወደ ፈጣሪ መሸኘት ነው።” (ቭላድምር ፑቲን)

የምዕራባውያንን እና የአሜሪካንን ግለሰብ ተኮር ፖለቲካ መከተል አስካላቆምን ድረስ እዚህች ሀገር ላይ ንጽሃን ዋስትና የላቸውም። ፍትህን ፈርጣማዎቹ እንደፈለጉ የሚዘውሯት ትሆናለች። ሆናለችም። ከስብዕና ወጥተው፣ ከፈጣሪ ተጣልተው በሰከረ ሰይጣናዊ ስርዓት ውስጥ ናቸው። ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ያጋባሉ፣ ሰይጣንን በአደባባይ ያመልካሉ፣ ሐውልት ይሰሩለታል። መፋታትን፣ ውርጃን፣ እብደትን ይደግፋሉ። ምክኒያቱም ከህብረተሰብ ይልቅ ግለኞች ናቸው።

ሩቅ ምስራቃዊያን ከዚህ ይልቅ ለህዝብ ጥቅም ስባል ጠንካራ የህግ ማዕቀብ ያላቸው ምስራቃዊያን ዛሬም በተሻለ ኑሮ፣ ጸጥታ ውስጥ ይኖራሉ። የህብረተሰቡ ግብረገብ ስብዕና እንደተጠበቀ ነው። ከስብዕና ወጥተህ እንደልብ መሆን አይቻልም። ህግ ይከበራል። ዲሞክራሲ ብሎ ያለገደብ መበልቀጥ የለም።#ወደምስራቅ_ተመልከቱ። ኢትዮጵያ ሆይ የምዕራቡ ዲሞክራሲ ይቅርብሽ።