ወጣትና ነገ

ወጣትነትን ብዙ ሰዎች በዕድሜ ገደብ ብቻ ይተረጉሙታል። ወጣትነትን ከስሜትና ከጉልበት አንጻርም ያገናኙታል። ለኔ ግን ወጣትነት ነገ ነው። አሁን ላይ ነገን የሚያይ፣ ለነገ የሚያስብ፣ ለነገ የሚሰራ፣ ለነገ የሚተጋ፣ ለነገው የሚዋጋ፣ ለነገው የሚሰዋ ነው። ነገ በህይወቱ የለለው ሽማግሌ ነው። ተስፋ የለለው ዛሬን ካደርኩ እግዚአብሔር ይመስገን፣ ለነገ እግዚአብሔር ያውቃል፣ ሰጽንክ ሰካ ዱክተረ አይነት የጨለመ ነብስ የሽማግሌ ነው።

ምን እያልኩ ነው?

ዛሬ ላይ ቆማችሁ ለነገ ምን ያህል ዋጋ ትከፍላላችሁ? ወጣትነት በውስጣችሁ አለ? ነገ ይታያችኋል? ነገን ዛሬ መስራት ጀምራችኋል? ስትማር፣ ስትሰራ፣ ስታቅድ፣ ስታልም፣ ስታሰላስል ነገን ከሆነ ለዚያ የሚያስከፍለውን ዋጋ ክፈል። ለዚያ ራዕይ እስከ መሰዋት ተንቀሳቀስ። ደራሽ በሆኑ ነገሮች መጓዝ ነገን ያራቁታል።

በፖለቲካው፣ በማህበራዊው፣ በኢኮኖሚው፣ በመንፈሳዊው እና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ስትሰማሩ ነገን ብቻ አስቡ። በተለይ ወጣቶች ሰልጥኑ፣ ተማሩ፣ ሩጡ፣ ተንቀሳቀሱ፣ አቅዱ፣ ታገሉ። አከባቢያችሁ፣ ሀገራችሁ፣ አፍሪካ እንዲሁም ዓለም እናንተን ትጠብቃለች። አሁን እኛ ያለንበት ወቅት የትላንት ውጠት ነው። ነገ ላለው ትውልድ የኛ ዛሬ ወሳኝ ነው። ዛሬ ባለህ አቅም ሁሉ ከሰራህ የነገው ትውልድ የተሻለውን ይኖራል

ሸኬን ሸናካን ዳምደክ
ወጣት ለነገው ይዋጋል

ውጊያው በእውቀትና በጥበብ ነው። ከአፈ-ሙዝ በሚሻል ስልት ነው።

ዛቤ